Search

ሕዝባችን የሰጠንን ታላቅ አደራ ተቀብለን የገባነውን ቃል በአግባቡ ለመወጣት ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ ነን፦ አቶ ሽመልስ አብዲሳ

ሰኞ መስከረም 18, 2019 179

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት ሆነው በድጋሚ የተመረጡት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጨፌ ኦሮሚያ 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት የመጀመሪያ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝብ ፍላጎቱን፣ ጥቅሙን እና ተስፋውን የገለጸበት ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ ምርጫ በዴሞክራሲ ባህላችን ግንባታ ሂደት ውስጥ እጅግ ወሳኝ እርምጃ ነበር ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ “ሕዝባችን የብልጽግና ፓርቲን በሙሉ ድምፅ በመምረጥ በፓርቲያችን ላይ ያለውን ታላቅ እምነት በግልጽ አሳይቷል” ሲሉ አክለዋል።

“ይህንን ትልቅ ዕድል ስለሰጠን ከምንም በላይ ይህንን ጀግና ሕዝብ በታላቅ አክብሮት ላመሰግን እወዳለሁ” ብለዋል።

ሕዝቡ ለብልጽግና ፓርቲ የሰጠውን ይህንን ትልቅ እና ከባድ አደራ ተቀብለው፣ የፓርቲው አመራሮች ሁሉ የገቡትን ቃል በአግባቡ ለመወጣት ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።

ጨፌ ኦሮሚያ ሕዝቡ በፓርቲው እና በአመራሩ ላይ ያሳየውን እምነት መሠረት በማድረግ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት በመሆን በዚህ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዲያገለግሉ ዕድሉን ስለሰጣቸው በታላቅ አክብሮት አመስግነዋል።

ይህንን አደራ በመቀበል ለኦሮሞ ሕዝብ ትግል ስኬት እና ዓላማዎች በሙሉ ቁርጠኝነት እና በከፍተኛ ብቃት እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል።

 

በዮናስ በድሉ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: