Search

የኦሮሚያ ክልል አዳዲስ ዞኖችን በማዋቀር አስተዳዳሪዎችን በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ መደበ

ሰኞ መስከረም 18, 2019 178
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በሥራ ላይ ባዋለው አዲሱ መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት በክልሉ ስድስት አዳዲስ ዞኖች አዋቅሯል።
እነዚህን አዳዲስ ዞኖች በበላይነት የሚመሩ አስተዳዳሪዎችን በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ በጨፌ ኦሮሚያ ሹመት ሰጥቷል።
በአዲሱ አደረጃጀት መሠረት የተቋቋሙት ስድስቱ ዞኖች ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን፣ ማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን፣ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን፣ የደቡብ ኦሮሚያ ዞን፣ ደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን እና የደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን ናቸው።
በዚህ መዋቅራዊ ሽግግር መሠረት አዲሶቹ ዞኖች ያቀፏቸው አካባቢዎች፦
ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ምስራቅ እና ምዕራብ ሀርጌ ዞኖችን ያካተተ ሲሆን፤ ደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ደግሞ አርሲ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምስራቅ ባሌ፣ የአሰላ ከተማ እና የዶዶላ ከተማን አቀፎ ተደራጅቷል።
ደቡብ ኦሮሚያ ዞን ቦረና፣ ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ቡሌ ሆራ ከተማ፣ ሞያሌ ከተማ እና የሻኪሶ ከተማን ሲያካትት፤ ደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን በበኩሉ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉ አባ ቦር፣ ጅማ፣ የአጋሮ ከተማ እና የመቱ ከተማን ይዞ ተዋቅሯል።
ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ እና የነጆ ከተማን ያካተተ ሲሆን፤ የማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን ደግሞ ምስራቅ ሸዋ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ምዕራብ ሸዋ እንዲሁም የአምቦ፣ የባቱ፣ የሆለታ፣ የሞጆ፣ የሰንዳፋ በኬ፣ የሸኖ እና የወሊሶ ከተማዎችን አካቶ በአዲስ መልክ ተደራጅቷል።
እነዚህን አዳዲስ ዞኖች በበላይነት እንዲመሩ በጨፌ ኦሮሚያ የተሰጡት አዳዲስ የሹመት ድልድሎች እንደሚከተለው ተከናውነዋል፦
• አቶ አብዱርራህማን አብደላ፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የምስራቅ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
• አቶ መስፍን መላኩ፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የምዕራብ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
• ዶ/ር ረሻድ ከማል፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
• ዶ/ር መንግሥቱ በቀለ፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
• አቶ አህመድ ኢድሪስ፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
• አቶ አህመድ ሀጂ፦ በምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የደቡብ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ
ይህ አዲስ መዋቅራዊ አደረጃጀትና የአመራር ድልድል የመንግሥትን አገልግሎት አሰጣጥ ለማፋጠንና የሕዝብን ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተገልጻል።
በሐይማኖት ከበደ
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: