የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ እና አምበሉ ያሬድ ባየህ ከነገው ጨዋታ በፊት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ “በሱዳኑ ጨዋታ የነበረብን አጋጣሚዎችን ያለመጠቀም ችግር የሚቀረፈው ትኩረት በማድረግ ነውና በዚያ ጉዳይ ላይ ተወያይተናል” ሲሉ ተናግረዋል።
ግብ የማስቆጠር ችግራችን የሚቀረፈው ተጫዋቾች በሚያድርባቸው የራስ መተማመን መሆኑንም ነው የገለፁት። “የእኛ ስራ ኳሱ ሳጥን ውስጥ እንዲደርስ እና አጋጣሚዎች እንዲፈጠሩ ማድረግ ነው” ሲሉም አክለዋል።
ለተጫዋቾችም ውሳኔ በመወሰን በኩል ነፃነት እንደተሰጣቸውም ተናግረዋል። “ሴኔጋል ትልቅ ቡድን ቢሆንም በህዝባችን ፊትና በሜዳችን ስለምንጫወት ባለ ድል ለመሆን ወደ ሜዳ እንገባለን። አሸናፊውን የ90 ደቂቃው ፍልሚያ ይወስነዋል” ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።
“በደጋፊዎቻችን ፊት መጫወት እጅጉን ይጠቅመናል ያለው” አምበሉ ያሬድ ባዬ በበኩሉ ሴኔጋልን ለማሸነፍ መዘጋጀታቸውን ገልጿል።
ስለተጫዋቾች አሁናዊ ሁኔታ የተጠየቁት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ መስፍን ታፈሰ እና በረከት ወልዴ ከነገው ጨዋታ ውጭ መሆናቸውን ተናግረዋል። መስፍን በቢጫ እንዲሁም በረከት በጉዳት ምክንያት ነው የማይሰለፉት።
በሀብታሙ ካሴ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: