Search

የኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት በአዲስ አበባ መከበር ጀመረ

ማክሰኞ መስከረም 19, 2019 99

ስድስተኛው የኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት ከመስከረም 19 እስከ መስከረም 21 ቀን በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል።

መርሐ ግብሩ የኦሮሚያን ተፈጥሮ፣ ባህል፣ ታሪክ እና የቱሪዝም ሀብቶች ለዓለም የሚያስተዋውቅበት መድረክ ነው።

በማስጀመሪያ መርሐግብሩ ላይ የተገኙት የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ የቱሪዝም ዘርፉን በቴክኖሎጂ በማዘመን ከዘመኑ ጋር አብሮ መሄድ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የዘንድሮው መርሐ ግብር ቱሪዝምን ከቴክኖሎጂ ጋር በማቀናጀት የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብት ከዓለም ጋር ለማስተሳሰር በር ከፋች መሆኑ ተጠቅሷል።

በመርሐግብሩ አጠቃላይ ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቁ እና በዲጂታል የበለጸጉ ድረ-ገጾች የተመረቁ ሲሆን፤ ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግሩ አሰራሮችም አስተዋውቀዋል።

በኤልሻዳይ ወንድማገኝ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: