የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደር መንግስት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ነው።
በጉባዔ ላይ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ወክለው የተመረጡ የምክር ቤት አባላት ተሳታፊ ናቸው፡፡
ምክር ቤቱ በዛሬው ጉባኤ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍና የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤ እና ምክትል አፈ ጉባኤ፣ የከተማ አስተዳደሩን ከንቲባ እና ምክትል ከንቲባ የመምረጥ እንዲሁም የፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመትን ጨምሮ የተለያዩ ሹመቶችን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: