የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ወ/ሪት ፈይዛ መሐመድ ዑመር የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደር መንግስት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤውን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በሚገኘው የምክር ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል።
ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው የተሰየሙት ወ/ሪት ፈይዛ መሐመድ ዑመር በምክር ቤቱ ፊት ተገኝተው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: