የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል ዋዜማን ምክንያት በማድረግ፣ “ኢሬቻ - ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ቃል 10 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው 2ኛው የኢሬቻ ታላቁ ሩጫ በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል።
የሩጫው ዓላማ ኢሬቻ የአንድነት፣ የወንድማማችነት እና የይቅርታ መድረክ መሆኑን ለዓለም በማስተዋወቅ ሳቢነቱን ማሳደግ እንደሆነ ተገልጿል።
በውድድሩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ አትሌቶች እየተሳተፉ ሲሆን ከ50 ሺህ በላይ ሰዎችም መሳተፋቸው ተጠቁሟል።
ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ የምስጋና፣ የዕርቅ፣ የፍቅር እና የአንድነት በዓል ከመሆኑ በላይ፣ የተለያዩ ብሔሮች እና ብሔረሰቦችን የሚያገናኝ እንዲሁም መግባባትን፣ ሰላም እና ወንድማማችነትን የሚያጠናክር የጋራ መድረክ እየሆነ መጥቷል።
በዓሉ የኦሮሞን ባህል እና እሴት ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማስተላለፍ ከማስቻሉም በላይ፣ በልዩነት ውስጥ መከባበርን እና ፍቅርን በማሳደግ፣ የኢትዮጵያ የጋራ ሀብት በመሆን ሀገራችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: