የሶማሊ ክልል ምክር ቤት 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ ዓመት የመጀመሪያ ጉባኤ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የቀረቡለትን አዳዲስ ተሿሚዎች ሹመት በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ በዛሬው ዕለት አጠናቋል።
በዕለቱ በተካሄደው መደበኛ ጉባኤ፣ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቅራቢነት ለተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች የቀረቡት ተሿሚዎች የሥራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት በምክር ቤቱ አባላት በጥብቅ ከተመረመረ በኋላ፣ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በታማኝነትና በትጋት ይወጣሉ በሚል ሙሉ እምነት ሹመታቸው አድቋል።
የተሾሙት አዳዲስ ኃላፊዎችም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው የተጣለባቸውን የሕዝብና የመንግሥት አደራ በቅንነት፣ በፍትሐዊነትና በግልጽነት ለመወጣት ቃል ገብተዋል።
ይህ አዲስ የተከናወነው የአመራር ድልድል በክልሉ የተጀመሩ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሰላም ማስከበር ሥራዎችን ይበልጥ ለማፋጠንና የመንግሥትን አገልግሎት አሰጣጥ ለማቀላጠፍ ያለመ መሆኑ ተገልጻል። በዚህም መሰረት፦
1. የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት፦ ዶ/ር ሁሴን አብዱላሂ
2. የሰላምና ጸጥታ ቢሮ፦ አቶ አብዲቃድር ረሺድ
3. የፋይናንስ ቢሮ፦ አቶ መሐመድ ሙሴ
4. የፍትሕ ቢሮ፦ አቶ ኸዲር አብዲራህማን
5. የግብርና ቢሮ፦ አቶ ጉሌድ አሕመድ
6. የትምህርት ቢሮ፦ አቶ መሐመድ ሼክ አደን
7. የክህሎትና ሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ፦ አቶ ፈይሰል ረሺድ
8. የጤና ቢሮ፦ ዶ/ር ሙሴ አሕመድ
9. የውኃ ቢሮ፦ አቶ ሲያድ ኑር
10. የእንስሳት ሀብት ቢሮ፦ አቶ ኢብራሂም ሐሰን
11. የገቢዎች ቢሮ፦ አቶ ሁሴን ጌይድ
12. የፕላን ቢሮ፦ አቶ ዑመር-ፋሩቅ ሐጂ ዋርፋእ
13. የንግድ ቢሮ፦ ወ/ሮ ሂቦ አሕመድ ዑመር
14. የሴቶች ቢሮ፦ ወ/ሮ ሐሊሞ ሐሰን
15. የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ፦ ወ/ሮ አያን አብዲ
16. የመስኖ ቢሮ፦ አቶ መሐመድ ፋታህ
17. የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ፦ ዶ/ር አብዲ አሕመድ
18. የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ፦ ወ/ሮ ኸድራ በሺር
19. የመንገዶች ቢሮ፦ አቶ ኢድሪስ ሙሴ
20. የከተማ ልማት ቢሮ፦ አቶ አሕመድ ሹክሪ
21. የፈጠራና ቴክኖሎጂ ቢሮ፦ አቶ መሐመድ አሊ ዳሂር
22. የአደጋ ስጋት አመራር ቢሮ፦ አቶ አሕመድ-ያሲን ሼክ ኢብራሂም
23. የማዕድንና ነዳጅ ቢሮ፦ ወ/ሮ ፋጡሞ አብዲራዛቅ
24. የባህልና ቱሪዝም ቢሮ፦ ወ/ሮ አያን መሐመድ
25. የማኅበራዊ ጉዳዮች ቢሮ፦ ኢንጂነር ሙህያዲን አብዲ
26. የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፦ መሐመድ ማህዲ
27. የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ፦ ወ/ሮ ሃኒ መሐመድ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: