Search

ኢትዮጵያ በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲዋ እንዲዘጋ ወሰነች

ሓሙስ መስከረም 21, 2019 128

10 የኤርትራ ዲፕሎማቶችም በ48 ሰዓታት ውስጥ ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ተወስኗል

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ እየፈጸመች ለምትገኘው ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ የትንኮሳ እና የጠላትነት እንቅስቃሴ ምላሽ ለመስጠት በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲውን ለመዝጋት መወሰኑን አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ በተጨማሪም የቪየና የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ኮንቬንሽንን በመጣስ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ ቀጥተኛ ስጋት በሚፈጥሩ ተግባራት ላይ በመሳተፋቸው በአዲስ አበባ የሚገኙ አስር የኤርትራ ዲፕሎማቶችን ተቀባይነት የሌላቸው (persona non grata) ሲል የፈረጃቸው ሲሆን፣ እነዚህ ዲፕሎማቶች በ48 ሰዓታት ውስጥ ከኢትዮጵያ ለቅቀው እንዲወጡ ማዘዙን ገልጿል።

ኢትዮጵያ የኤርትራ መንግሥት በሉዓላዊ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ከሚመሩ መርሆዎች ጋር የሚቃረኑ ማናቸውንም ድርጊቶች እንዲያቆም አሳስባለች።

ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ያላትን ጠንካራ የታሪክ፣ የባህል እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ትልቅ ዋጋ የምትሰጥ መሆኗን የጠቆመው ሚኒስቴሩ፣ ሁልጊዜም ቢሆን ለሰላማዊ አብሮ መኖር፣ ለቀጠናዊ መረጋጋት እና ትስስር ቅድሚያ ስትሰጥ መቆየቷን አብራርቷል።

ኢትዮጵያ ለውዝግቦች ሰላማዊ መፍትሔ ለመስጠት እና ዘላቂ ሰላምን፣ ደህንነትንና ቀጣናዊ ትስስርን ለማስፈን ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ጋር በትክክለኛው ቁርጠኝነት መስራቷን እንደምትቀጥልም አረጋግጧል።

#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: