Search

የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶች

ሓሙስ መስከረም 21, 2019 111

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚከበረውን የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ አስታወቀ።

ነገ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ መርሐ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ፡-

◉ ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ (22 ወይም ጎላጎል አደባባይ ላይ እና ታች)

◉ ከአድዋ ድልድይ ወደ ዘሪሁን ህንፃ እና ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ)

◉ ከአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ (ፒኮክ መብራት)

◉ ከቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ ወደ መስቀል አደባባይ (ወሎ ሠፈር አደባባይ ላይ እና ታች)

◉ ከጋዜቦ አደባባይ በደንበል ህንፃ ጀርባ ወደ ፊላሚንጎ እንዲሁም ከጋዜቦ አደባባይ በአዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር መብራት (ጋዜቦ አደባባይ)

◉ ከቅዱስ ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር መብራት (ቅዱስ ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ መብራት)

◉ ከቀድሞው ብርሃን ኢትዮጵያ መስቀለኛ በአዲሱ መንገድ ወደ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን (ብርሃን ኢትዮጵያ መስቀለኛ)

◉ ከአፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (አፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ)

◉ ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (አፍሪካ ህብረት መብራት)

◉ ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ)

◉ ከሜክሲኮ አረቁ ፋብሪካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (አረቄ ፋብሪካ መስቀለኛ)

◉ ከሰንጋ ተራ 40/60 ቤቶች መገንጠያ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መገንጠያ)

◉ ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ  ብሔራዊ ቴአትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)

◉ ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ  ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትዮሮሎጂ መታጠፊያ)

◉ ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኤሚግሬሽን መብራት ( ጥቁር አንበሳ መስቀለኛ)

◉ ከጎላ ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኤሚግሬሽን መብራት (ጎላ ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ)

◉ ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ኤሚግሬሽን መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ)

◉ ከንግድ ማተሚያ መታጠፊያ ወደ ፍል ውሃ መስቀለኛ (ንግድ መታጠፊያ)

◉ ከፓርላማ መብራት ወደ ውጭ ጉዳይ (ፓርላማ መብራት ላይ)

◉ ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ)

ከረፋዱ 4:00 ሠዓት ጀምሮ የሚዘጋ ሲሆን አሽከርካሪዎች አስቀድመው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እያሳሰበ ከንጋቱ 12:00 ሠዓት ጀምሮ በተጠቀሱት መንገዶች ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ ማቆም የተከለከለ መሆኑን አሳስቧል።

ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ ጥቆማ ለመስጠት በ01-11-11-01-11 እና በ990 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም እንደሚቻል ፖሊስ  መልዕክቱን አስተላልፏል።

#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ See less

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: