Search

በተለያዩ ዘርፎች የክልሉን ልማት የሚያጠናክሩ እና የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎች ላይ ትኩረት ይደረጋል - ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)

ቅዳሜ መስከረም 23, 2019 131

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የክልሉን ልማት የሚያፋጥኑ ተግባራት እንደሚከናወኑ አረጋግጠዋል።

በተለይም በሰላም እና ደኅንነት፣ በምግብ ሉዓላዊነት፣ በገጠር ሽግግር እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን በማፋጠን እንዲሁም በሰው ኃይል፣ በትምህርት፣ በጤና እና በማኅበራዊ ልማቶች ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሠራ ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ብልሹ አሠራርን በመከላከል ረገድ ክልሉ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በትኩረት እንደሚሠራ ዶክተር የትምጌታ ገልጸዋል።

እነዚህን ዕቅዶች ለማሳካት እና የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጠንክረው እንደሚሠሩ ያረጋገጡት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራም አብራርተዋል።

"የክልሉ ሕዝብ የሰጠንን አደራ በትጋት እና በቅንነት በማገልገል የበኩላችንን እንወጣለን" ሲሉም አክለዋል።

በአባዲ ወይናይ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: