Search

በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች የተገነቡ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላለፉ

ቅዳሜ መስከረም 23, 2019 138

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች የተገነቡ ዘመናዊ የጡብ መኖሪያ ቤቶች ተመርቀው በዛሬው ዕለት ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል።

በብርብር ከተማ አስተዳደር ደልቦ ቀበሌ የተገነቡት እነዚህ መኖሪያ ቤቶች፤ ከጋጮ ባባ ወረዳ በአደጋው ምክንያት ለተፈናቀሉ 100 አባወራዎች የተላለፉ ሲሆን፣ በአጠቃላይ 595 የቤተሰብ አባላትን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ደምሴ አድማሱ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የገጠር ሽግግር ስትራቴጂን መሠረት በማድረግ የተገነቡት አዲሶቹ የመኖሪያ ቤቶች፤ በአደጋው የተጎዱ ወገኖችን ዘላቂ የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻልና መልሶ ለማቋቋም ከተከናወኑ የልማት ሥራዎች አካል መሆናቸው በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።

በትዕግስቱ ቡቼ

#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: