ኢትዮጵያ ያካሄደችውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ በዛሬው ዕለት አዲስ የመደመር መንግሥት ምሥረታ በይፋ ይካሄዳል።
በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲሆን ተጠሪነቱም ለሀገራችን ሕዝብ መሆኑ ተደንግጓል።
በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 የምክር ቤቱ የሥራ ዘመን በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀመር በተደነገገው መሠረት፣ የመንግሥት ምሥረታ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ይከናወናል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: