አዲስ መንግሥት፣ አዲስ አቅጣጫ፣ አዲስ ተስፋ በሚል መሪ ጽንሰ-ሀሳብ የሚገለጸው ይህ ታሪካዊ ምዕራፍ፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ ላቀ የስልጣኔ ማማ፣ ዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና ለመሸጋገር የያዘችውን ፅኑ ሀገራዊ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።
ከታሪካዊው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ የሚመነጨው ይህ አዲስ አቅጣጫ፣ የሕዝባችንን የነገ ብሩህ ተስፋ በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባትና የሀገር በቀል ልማት ስትራቴጂዎቻችንን በላቀ የውጤታማነት ደረጃ ለማስቀጠል የተቀረፀ ታላቅ ራዕይ ነው።
ይህ የታደሰ ጉዞ በሁሉም የልማት መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችን ይበልጥ በማጠናከር፣ ተቋማዊ አቅምን በማጎልበት እና የዜጎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ወደ ተጨባጭ ተግባር ይቀየራል።
የሕዝባችንን አንድነትና ጥንካሬ አስተባብሮ በመያዝ፣ በጋራ ጥረትና በማይበገር ቁርጠኝነት ወደፊት መራመድ የነገዋን የበለፀገችና የታፈረች ኢትዮጵያን እውን የማድረጊያ ዋነኛ ቁልፍ ነው።
በአዲስ ተስፋና በጠራ አቅጣጫ ኢትዮጵያን እንገነባለን!
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: