Search

አዲስ ነገር ዕዳም ምንዳም ያለው በመሆኑ ለሀገራችን የሚበጀውን መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሰኞ መስከረም 25, 2019 90

አዲስ ነገር ዕዳም ምንዳም ያለው በመሆኑ ለሀገራችን የሚበጀውን መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ዜጋ እንደማይኖራትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሰየሙ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ 7ኛውን ምርጫ በቀላሉ እንዳልመረጠ ጠቁመዋል።

ነገር ግን ህልውናውን ለማጽናት ፈተናዎችን ሁሉ በጽናት አልፎ ውሳኔውን ማሳወቁን እና በዚህም ጠንካራ የመንግሥት ሥርዓት ለመሥራት የሚያስችል መሠረት መጣሉን ገልጸዋል።

ዓለም በተለያየ መልኩ እየተቀያየረች እና አይገመቴነት በሰፈነበት በአሁኑ ወቅት ሀገራችንን በጽኑ መሠረት ላይ ማቆም ወሳኝ ሥራ መሆኑን ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ማንኛውም አዲስ ነገር ዕዳም ምንዳም ያለው በመሆኑ ለሀገራችን የሚበጀውን መርጦ መከተል የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ዓለም በርካታ የኢንዱስትሪ አብዮቶችን ሲያሳልፍ ለሀገራችን የደረሳት ትራፊው ብቻ እንደነበር ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እንደ ሀገር ቀድሞ ካለመዘጋጀት የሚመጣውን ችግር ለመቋቋም አሁናዊ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!

በለሚ ታደሰ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: