የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማሕሙድ አሊ የሱፍ፣ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለተጨማሪ አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው የተሰማቸውን ላቅ ያለ ደስታ ገልጸው፣ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተልፈዋል።
ሊቀመንበሩ በመልዕክታቸው፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት መቀመጫ እና የአህጉሪቱ ዲፕሎማሲያዊ መዲና እንደመሆኗ መጠን፣ በአህጉራዊው ቤተሰብ ውስጥ ልዩ ስፍራ እንዳላት ገልጸዋል።
አክለውም የአፍሪካን ውህደት፣ ሰላም፣ ደኅንነት እና የልማት አጀንዳዎችን ለማስፋፋት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከካቢኔያቸው ጋር በቅርበት የመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው አረጋግጠዋል።
#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: