Search

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በሁለቱ ምክር ቤቶች ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

ማክሰኞ መስከረም 26, 2019 113

 

✍🏽ምክር ቤት አባላት የመንግሥት ሥልጣን ምንጭ የሆነውን የሕዝብ ውክልና በመያዝ መልካም አስተዳደርን የማስፈን፣ የኑሮ ውድነትን የመግራት፣ የምርት ዕድገትን የማረጋገጥ፣ እንዲሁም ሰላም እና ደኅንነትን የማጽናት ታሪካዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

✍🏽ሀገራዊ የሰብል ምርት ወደ 1.3 ቢሊዮን ኩንታል ማደጉ፣ የወጪ ንግድ ገቢ 11.2 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት 4.5 ቢሊዮን ዶላር መመዝገቡ፣ አጠቃላይ የታክስ ገቢ 1.18 ትሪሊዮን ብር መድረሱ እና የዋጋ ግሽበት ወደ 13.4 በመቶ ዝቅ ማለቱን አንስተዋል።

✍🏽ጊዜ እና ሀብት ያባክኑ የነበሩ የቆዩ ፕሮጀክቶችን ፈጥኖ ማጠናቀቅ መቻሉ፣ እንዲሁም የከተማ ኮሪደር ልማትና የአረንጓዴ ዐሻራ ፕሮጀክቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ አብነት የሚሆኑ ስኬቶች ሆነው መመዝገባቸው ጠቅሰዋል።

✍🏽 የጠመንጃ ባህል እና የነፍጥ አዙሪትን በዘላቂነት በማስቀረት የፖለቲካ ልምምዱን በሰላም፣ በንግግር እና በመደማመጥ ላይ መመሥረት፤ እንዲሁም በሀገራዊ ምክክር ሂደት የተገኙ የውይይት ውጤቶችን ወደ ተግባር ለመቀየር ቅድሚያ ተሰጥቷል።

✍🏽 የውጭ ግንኙነት ፖሊሲው ሀገራችንን ከተቀባይነት ወደ ተጽዕኖ ፈጣሪነት እያሸጋገራት መሆኑ፣ እንዲሁም አስተማማኝ የባሕር በር ለማግኘት የሚደረገው ጥረት በሰላማዊ መንገድና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሠረተ መሆኑ ተብራርቷል።

✍🏽 ሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገቱን 10.1 በመቶ ማድረስ፣ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን 65 በመቶ፣ የጤና መድኅን ሽፋንን 85 በመቶ፣ የተማሪዎች ምገባ ሽፋንን 70 በመቶ ማድረስ፣ እንዲሁም የዋጋ ግሽበትን ወደ ነጠላ አሃዝ ዝቅ ማድረግ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

✍🏽 ኢትዮጵያ ኃላፊነት የወሰደችበትን 32ኛውን የዓለም አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP 32) በተሳካ ሁኔታ ለማዘጋጀት፣ እንዲሁም በበጀት ዓመቱ ከ1.6 ሚሊዮን በላይ የውጭ ቱሪስቶችን ለመሳብ ግብ መቀመጡን ገልጸዋል።

✍🏽የተጀመረውን የፀረ-ሙስና እና ሌብነት ትግልን አጠናክሮ መቀጠል፣ የመከላከያ እና የጸጥታ ተቋማትን አቅም መገንባት፣ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት ቅንጅትን ማሳለጥ፣ እንዲሁም የታክስ አስተዳደርን በማዘመን የመንግሥትን ወጪ እና ገቢ በአግባቡ መቆጣጠር የመንግሥት አቅጣጫ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ አንስተዋል።

#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!

በለሚ ታደሰ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: