Search

የኢፌዴሪ 7ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ1ኛ ልዩ ስብሰባው በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ እየተወያየ ነው

ረቡዕ መስከረም 27, 2019 238

7ኛው የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 1ኛ ልዩ ስብሰባው በፌደራል መንግስት አስፈጻሚ አካላት ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ እየመከረ ይገኛል።

የምክር ቤት አባልና የመንግሥት ተወካይ የተከበሩ አቶ ፍቃዱ ከተማ በረቂቅ አዋጁ አስፈላጊነት ላይ አጭር ማብራሪያ አቅርበዋል።

በቀረበው ማብራሪያም ከዚህ በፊት በነበሩት 22 አስፈፃሚ አካላት ላይ የቁጥር ልዩነት እንደሌለና ከቁጥር አንፃር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በነበሩበት 22 ሆነው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

ይህም ሆኖ በሁለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ላይ ብቻ የስያሜ ለውጥ መደረጉንና ሁለት ሚኒስቴሮች አንደ አዲስ መቋቋማቸው ተብራርቷል።

እንደ አዲስ የተቋቋሙት ሁለት ሚኒስቴር መ/ቤቶች ቀድሞ "የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር" የነበረው በአዲሱ "የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር" በሚል እና ቀድሞ "የቱሪዝም ሚኒስቴር" የነበረው በአዲሱ "የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር" በሚል መቋቋማቸው ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ቀድሞ "የፕላንና ልማት ሚኒስቴር" የነበረው "የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር" በሚል እና ቀድሞ "የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር" የነበረው "የሎጂስቲክስ ሚኒስቴር" በሚል ስያሜያቸው መቀየሩ ተገልጿል።

በሚኒስቴር መ/ቤቶቹ ላይ ማሻሻያው ያስፈለገበት ምክንያት ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እና ከተልዕኳቸው ጋር ለማጣጣም መሆኑም ተብራርቷል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ክብርት ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ለምክር ቤቱ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እያቀረቡ እንደሚገኙ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እንደ አዲስ በተቋቋሙት ሁለቱ ሚኒስቴር መ/ቤቶችም ሆነ የስያሜ ለውጥ በተደረገባቸው ሁለቱ ሚኒስቴር መ/ቤቶች ዙሪያ በቀጣይ ሰፋ ያለ ትንታኔ ይዘን የምንቀርብ ይሆናል።

#የመደመርመንግሥት

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: