Search

ኢትዮጵያና ናይጄሪያ ሁለገብ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

ረቡዕ መስከረም 27, 2019 105

ኢትዮጵያና ናይጄሪያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ በሥርዓተ-ምግብ ዙሪያ የልምድ ልውውጥ ለማድረግና ሁለገብ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከናይጄሪያ ፌዴራል ሪፐብሊክ ምክትል ፕሬዝዳንት ሴናተር ካሺም ሼቲማ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ሁለቱ ወገኖች በስትራቴጂካዊ አጋርነት የተሳሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ያላቸውን ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ አቅም በተቀናጀ መልኩ በመጠቀም አፍሪካን በተሻለ መንገድ ለመቅረጽ የሚያስችል ታላቅ አቅም እንዳላቸውም አስረድተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ፣ ናይጄሪያ በኢትዮጵያ በሰቆጣ ቃል ኪዳን መርሃ-ግብር የተገኘውን ተጨባጭ ስኬት በመገንዘብ በልዑካን ቡድኗ በኩል ላደረገችው ጉብኝት ምስጋና አቅርበዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንት ሴናተር ካሺም ሼቲማ በስራ ላይ ባሉበት አካባቢ የሥርዓተ-ምግብን ለማሻሻል የሚያሳዩት ቁርጠኝነት ለአህጉሩ አርአያ የሚሆን መሆኑን አመልክተዋል።

በሌላ በኩል በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ኢትዮጵያ የዲፕሎማቲክና የሰርቪስ ፓስፖርት ለያዙ የናይጄሪያ ዜጎች የቪዛ ነፃ የጉዞ ሥርዓትን በሥራ ላይ ማዋሏንና የአሠራር ማሻሻያ ማድረጓን ጠቁመዋል።

በኢንቨስትመንት ዘርፍም የናይጄሪያው ባለሀብት አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ ልማት ውስጥ እያበረከቱ ያሉትን ጉልህ አስተዋጽኦ አንስተው ያወሱ ሲሆን፣ በቀጣይም ሌሎች የናይጄሪያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች መሰማራት በሚችሉበት ሰፊ ዕድል ላይ ተወያይተዋል።

‎#የመደመርመንግሥት

#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!

 

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: