የኢፌዲሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አዲሷ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከቀድሞው የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ከተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር ጋር የሥራ ርክክብ አደረጉ።
በሥራ ርክክቡ ወቅት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንዳስታወቁት፣ ምክር ቤቱ የጀመረውን የሪፎርም ሥራ በማጠናከር ተቋሙ የተሰጠውን ሕገ መንግሥታዊ ኃላፊነት በብቃት እንዲወጣ ትኩረት ሰጥተው ይሠራሉ።
አፈ ጉባኤዋ አክለውም ብሔራዊ አንድነትን እና ዘላቂ ሰላምን ማጠናከር፣ ውጤታማ የፊስካል ሽግግርን እና ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍልን ማረጋገጥ እንዲሁም የሕገ መንግሥት የበላይነትን ማስከበር ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎቻቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው የተሰየሙት አቶ ደስታ ሌዳሞ ከምክር ቤቱ የቀድሞ ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ዛሀራ ሁመድ ጋር የሥራ ርክክብ ፈጽመዋል።
አቶ ደስታ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፣ ኅብረብሔራዊነትን እና አብሮነትን ማጎልበት፣ ዲሞክራሲያዊ መግባባትን ማጠናከር እንዲሁም በቀድሞው አመራር የተጀመሩ የተቋሙን ተልዕኮዎች በተቀናጀ መልኩ ማስቀጠል ትኩረት ከሚሰጣቸው የሥራ አቅጣጫዎች መካከል መሆናቸውን ማስገንዘባቸውን ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#የመደመርመንግሥት #ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: