Search

የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላለፉ

ረቡዕ መስከረም 27, 2019 56

የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ፕሬዚዳንት ሼህ ሙሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን፣ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዳግም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በተመሳሳይ የሀገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዱባይ ገዥ ሼህ ሙሐመድ ቢን ራሺድ አል ማክቱም፤ እንዲሁም ምክትል ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የፕሬዚዳንታዊ ጽ/ቤት ሊቀመንበር ሼህ መንሱር ቢን ዛይድ አል ናህያን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመሳሳይ የደስታ መግለጫ መልዕክት መላካቸውን ኤምሬትስ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

#የመደመርመንግሥት

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: