የመደመር መንግሥት ለቱሪዝም ዘርፍ በሰጠው የላቀ ትኩረት እና በወሰዳቸው ስትራቴጂያዊ ውሳኔዎች ዘርፉ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት ዋና ሞተር እና ከዋነኞቹ የውጭ ምንዛሬ ማስገኛዎች መካከል እየሆነ ይገኛል።
ባለፉት አምስት ዓመታት የተፈጥሮ፣ የባህል እና የታሪክ ሀብቶችን የሸፈነውን አቧራ በማራገፍ ወደ ላቀ ኢኮኖሚያዊ ሀብት በመቀየር ኢትዮጵያ አዲስ የቱሪዝም ዘመን እንድትጀምር ተደርጓል።
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በሕዝብ ተወካዮች እና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት በቱሪዝም ዘርፍ ያስመዘገበችውን የላቀ ውጤት ገልጸዋል።
በንግግራቸውም እንደተገለጸው በከተሞች የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች፣ የገበታ ለሸገር፣ የገበታ ለሀገር እና የገበታ ለትውልድ ሜጋ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ማራኪ እና ተወዳዳሪ አዲስ የቱሪዝም መዳረሻ አድርገዋታል።
ባለፉት 5 ዓመታት በተከናወኑት የተቀናጁ የልማት ሥራዎች የውጭ እና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እንዲያድግ ተደርጓል።
በተለይም በገበታ ለሀገር መርሐ ግብር የተገነቡት የጎርጎራ፣ ወንጪ፣ ኮይሻ እና ሀላላ ኬላ ፕሮጀክቶች ከመጠናቀቃቸው ባሻገር በአዲስ አበባ እና በሌሎች ዋና ዋና ከተሞች የተከናወኑት የኮሪደር ልማቶች ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የቱሪዝም ካርታ ላይ በጉልህ ቦታ አስቀምጠዋል።
እነዚህ ከተማን የማዘመን እና የመዳረሻ ልማት ሥራዎች በበርካታ ዓለም አቀፍ ተጓዦች፣ የከተሞች ከንቲባዎች እና የሀገር መሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ዕውቅና በማግኘት እንደ አብነት የሚጠቀሱ ስኬቶች ለመሆን በቅተዋል።
በያዝነው በጀት ዓመት መንግሥት ለዘርፉ የሰጠውን ልዩ ትኩረት አጠናክሮ በመቀጠል ከ1.6 ሚሊዮን በላይ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ አቅዶ በትጋት በመሥራት ላይ ይገኛል።
ይህ ታላቅ ዕቅድ ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ ለማስመዝገብ ካቀደችው የ10.1 በመቶ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ግብ ጋር በተቀናጀ እና በተጣጣመ መንገድ የሚተገበር ይሆናል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ በጥሩ ዝግጅት እንድታስተናግድ ኃላፊነት የተሰጣትን 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) ዝግጅት በስኬት ለማጠናቀቅ በይዘትም ሆነ በመሰናዶ በከፍተኛ ትጋት እየተሠራ ይገኛል።
ይህ ታላቅ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ የስብሰባ ቱሪዝም (MICE Tourism) ያላትን ዝግጁነት፣ ዘመናዊ የመሰረተ ልማት አቅም እና ተፈጥሯዊ ማራኪነት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተግባር የሚያሳይ ትልቅ መድረክ ይፈጥራል።
በሜሮን ንብረት
#የመደመርመንግሥት
#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: