የጃማይካው ጠቅላይ ሚኒስትር አንድሩ ሆልነስ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ዳግም ለተመረጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም፣ ጃማይካ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የቆየ ወዳጅነት እና ጠንካራ የሕዝብ ለሕዝብ ቁርኝት ከፍተኛ ዋጋ እንደምትሰጠው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በቅርቡ በጃማይካ በሜሊሳ አውሎ ነፋስ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች የሚገመግም የቴክኒክ ቡድን በመላክ ላሳየችው አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት እና የባለብዙ ወገን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
በመጨረሻም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስኬታማ የሥራ ዘመን እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዘላቂ ብልጽግናን ተመኝተዋል።
#ትልቅ_ሀገር! #ትልቅ_ሕዝብ! #ታላቅ_ርዕይ!
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: