የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሕንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ሱብራማኒያም ጃይ ሻንካር ጋር በጽሕፈት ቤታቸው በሁለትዮሸ እና በወቅታዊ ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
ሚኒስትሮቹ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በትምህርት እና ባህል፣ ንግድ እና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በዲጂታይዜሽን ዙሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን የበለጠ ለማስፋት እና ለማጠናከር መክረዋል።
የሕንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቅርቡ በሕንድ አስተናጋጅት በተካሄደው የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ ኢትዮጵያ ለነበራት ውጤታማ ተሳትፎ ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: