Search

የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ

ዓርብ መስከረም 29, 2019 89

የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የስራ ጉብኝት አደረጉ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ለፕሬዝዳንቱ አቀባበል አድርገዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በጉብኝቱ ወቅት ኢንስቲትዩቱ በአገልግሎት፣ በግብርና፣ በጤና፥ በትምህርት  እና በሌሎች ዘርፎች  የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት ቴክኖሎጂ የምርምር እና ልማት ስራዎች ያስመዘገባቸዉን ስኬቶች ገለፃ ሰጥተዋል። 

በተጨማሪም ኢንስቲትዩቱ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕይን ለማሳካት እያከናወነ የሚገኘውን የቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት ስራዎችን በተመለከተ አብራርተዋል።

ፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ ጉብኝቱን አስመልክቶ ኢትዮጵያ ለኤ. አይ ቴክኖሎጂ የሰጠቸው ትኩረት ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ አርዓያነት ያለው ስራ መሆኑን ገልጸዋል።

የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር ለአፍሪካ የሚተርፍ መፍትሄ እንዳለው መናገራቸውን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#የመደመርመንግሥት 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: