Search

በመሶብ የአንድ ማዕከል ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት በመስጠት 99.6% የተገልጋይ እርካታ ማስመዝገብ ተችሏል፡- የከንቲባ ጽ/ቤት

ቅዳሜ መስከረም 30, 2019 94
በመሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አግልግሎት ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት በመስጠት 99.6% የተገልጋይ እርካታ ማስመዝገብ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው፣ የሕዝብ ተሳትፎንና ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ ቀልጣፋ አስተዳደር በመዘርጋት፣ የነዋሪዎቿን ሁለንተናዊና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በበጀት ዓመቱ አንደኛ ሩብ ዓመት ጠንካራ የተቋም ግንባታን ቁልፍ ሥራ አድርጎ በመስራት ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡
የአገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነታቸው እየተመዘነ አገልግልት በሚበዛባቸው ተቋማት ላይ የሪፎርም ሥራ መተግበሩን የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፣ በዚህም ሥራና ሠራተኛን በማገናኘት፣ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ቀጣይነት ያለው ለውጥ እየተመዘገበ ይገኛል ብሏል።
ተገልጋዮችም በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎና ባለቤትነት እንዲኖራቸው በተዘረጋው አሠራር ሌብነትንና ብልሹ አሠራርን በመቀነስ ግልጽነትና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን መሠረት ተጥሏል።
የስታንዳርዳይዜሽን ትግበራ በ78 ተቋማት ላይ ክትትል እና ደጋፍ በማድረግ በተገኙ ክፍተቶች ሊይ በግብረ-መልስ እየታረመ ይገኛል፡፡
የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤቱን ጨምሮ በ11 ክፍለ ከተሞች ቀልጣፋ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑም ተገልጿል።
በመሶብ የአንድ ማዕከል እስካሁን ለ1 ሚሊዮን ተገልጋዮች ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት በመስጠት 99.6% ከፍተኛ የተገልጋይ እርካታ ማስመዝገብ ተችሏልም ነው ያለው።
ከዚህ በፊት ዲጂታል ተደርገው የነበሩ 392 አገልግሎቶችን የማጥራት ሥራ በመሥራት በተገቢ ሁኔታ እየተሰጡ መሆናቸውና ወደ አዲስ መሶብ ዲጅታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ እንዲገቡ 324 አገልግልቶች መለየታቸው ተመላክቷል።
በሩብ ዓመቱ ወደ አዲስ መሶብ ማዕከል ገብተው አገልግልት እንዱሰጡ ከተለዩት 30 ዋና ዋና አገልግልቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ትግበራ እንዱገቡ መደረጉን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: