Search

አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን 2 ለ 1 አሸነፈ

ቅዳሜ መስከረም 30, 2019 133
በስድስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በኢሚሬትስ ስታዲየም ሊድስ ዩናይትድን ያስተናገደው አርሰናል 2 ለ 1 አሸንፏል።
ሊድስ ዩናይትድ 55ኛው ደቂቃ ላይ ጀምስ ጀስቲን ባስቆጠራት ግብ ጨዋታውን መምራት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም፣ 62ኛው ደቂቃ ላይ ሪካርዶ ካላፊዮሪ እንዲሁም 70ኛው ደቂቃ ላይ ብሩኖ ጊማሬሽ ያስቆጠሯቸው ግቦች አርሰናልን ባለ ድል አድርገዋል።
ውጤቱን ተከትሎ በሰንጠረዡ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አርሰናል ነጥቡን 15 ያደረሰ ሲሆን፣ በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተረታው ሊድስ ዩናይትድ በ9 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: