በፖርቹጋል በተካሄደው የሊዝበን ማራቶን የሴቶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ያሉትን ደረጃዎች ይዘው በመግባት አሸንፈዋል።
አትሌት መስከረም ማሞ ርቀቱን 2 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ከ04 በመጨረስ ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ፤ አትሌት ጠጅቱ ስዩም ደግሞ በ7 ማይክሮ ሰከንድ ዘግይታ ሁለተኛ ሆናለች።
አትሌት በሻንኬ ኢሙሼ፣ አትሌት ስንታየሁ ጥላሁን እና አትሌት አበበች አፈወርቅ ከሦስት እስከ አምስት ያሉትን ደረጃዎች በመያዝ በሊዝበን ጎዳናዎች የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ አድርገውል።
በወንዶች ዘርፍ አትሌት ደሳለኝ ይሌ አራተኛ ሲወጣ፣ አትሌት አብዲ አሊ እና አትሌት ደምሱ ገመዳ ሰባተኛ እና ስምንተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: