የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የ2019 ዓ.ም 19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ይገኛል።
ቀኑን አስመልክቶ ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፣ ሰንደቅ ዓላማችን የጋራ ማንነታችን፣ የሉዓላዊነታችን አርማና የአንድነታችን ምልክት ነው።
ልዩነቶቻችንን በውይይት እንፍታ፤ አንድነታችንን በመግባባት እናጠናክር፤ ሀገራችንንም በጋራ ጥረት እንገንባ ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ ዛሬ ሰንደቃችንን ከፍ ስናደርግ፣ ነገ የኢትዮጵያን ክብር፣ ሰላምና ብልጽግና ከፍ ለማድረግ ቃል እንግባ ብለዋል።
ኢትዮጵያ በዜጎቿ አንድነት ትጠናከራለች፤ በጋራ ቁርጠኝነታችንም ለትውልድ ትጸናለች ሲሉም አጽንዖት ሰጥተዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: