የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የሴካፋ የመጀመርያ ማጣሪያ ጨዋታውን ከቡሩንዲ ጋር አድርጎ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም በተደረገው በዚህ ጨዋታ የኢትዮጵያን የማሸነፊያ ግቦች ዘሚካኤል ምንያህል፣ አክረም አብዱሰላም እና አብዲሳ ጉተማ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ያደረገው ጨዋታ የምድቡ የመጀመርያው መርኃ ግብር ነው፡፡
በአሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች በሔራዊ ቡድን ከሁለት ቀናት በኋላ ከዩጋንዳ አቻው ጋር ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ያከናውናል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: