Search

የድል ሠራዊት፡ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና የትውልድ ተስፋ ዋስትና

ማክሰኞ ጥቅምት 03, 2019 45

ታሪክ ይሠራል፤ ይደገማልም። ነገር ግን ታሪክን ልሥራ ያለው ሁሉ አይሠራውም።

ታሪክን የሚሠሩት፣ ዋጋ የሚከፍሉት እና በደማቸው እና በአጥንታቸው የኢትዮጵያን ነፃነት ለማስጠበቅ የቆሙት እውነተኛ ጀግኖች ናቸው።

ዛሬም እንደ ትናንቱ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና አንድነት ጽንቶ የቆመው በአንድ ታላቅ ኃይል ነው፤ እርሱም አሸናፊነት ማንነቱ በሆነው የድል ሠራዊት ነው።

ይህ የሕዝብ ደንካራ ጋሻ፣ የሰላም ዘብ እና ድል አብሳሪ የሆነ ሠራዊት ነው። በየግንባሩ እና በየታሪክ ምዕራፉ የተጎናጸፋቸው አንጸባራቂ ድሎች የዕድል ወይም የአጋጣሚ ውጤቶች አይደሉም።

ይልቁንም ከዓድዋ እስከ ወቅቱ የሉዓላዊነት ማስከበር ግጥሚያዎች ካለፈው ትውልድ የወረሰው የጀግንነት እሴት፣ የላቀ ወታደራዊ ሥነ-ምግባር እና ለሕዝብ እና ለሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ ካለው ፍጹም ታማኝነት የሚመነጩ የቁርጠኝነት ውጤቶች ናቸው።

የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች የኢትዮጵያን አንድነት ለማፍረስ እና ሕዝብን ለመበተን እጃቸውን በዘረጉ ቁጥር፣ ይህ የድል ሠራዊት እንደ ብረት የጠነከረ ማሸነፊያ ግንብ ሆኖባቸዋል።

ጀግናው ሠራዊት ምቹ ባልሆነ የአየር ንብረት፣ በተራራማና በተለያዩ አስቸጋሪ መልክዓ-ምድራዊ ፈተናዎች ውስጥ አልፎ ድልን የመጨበጥ ጥበብ ያለው ዘመናዊ እና ስትራቴጂያዊ ኃይል ነው።

ሠራዊቱ በመልካም ስብዕና እና በኢትዮጵያዊነት ሥነ-ልቦና የታነጸ በመሆኑ፣ የጠላትን የክፋት ሴራ ሁሉ እያመከነ የነፃነታችን እና የፅናታችን ግንባር ቀደም ምልክት ሆኖ ቀጥሏል።

የሠራዊታችን ድል በጦር ሜዳ ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ እርሱ የሕዝብ አለኝታ፣ የልማት አጋር እና የሰላም ዋስትና ጭምር ነው።

በታላላቅ የልማት ሥራዎች፣ በፈታኝ አደጋዎች እና በሰላም ማስከበር ስምሪቶች በሄደበት ሁሉ ፍቅርን እና ሰላምን ይዘራል፤ ሕዝብን ከጥፋት ኃይሎች ይታደጋል።

ዛሬ እያስመዘገባቸው ያሉ አንጸባራቂ ድሎች የኢትዮጵያን ክብር ከመጠበቅ ባለፈ፣ ቀጣዩ ትውልድ በኩራት እና በነፃነት የሚኖርባትን ጠንካራ እና የበለጸገች ምድር እየገነባ ይገኛል።

አሸናፊነት በደሙ ውስጥ የሚዘዋወር፣ ሽንፈትን የማያውቅ እና ሁልጊዜም ለሕዝብ እና ለሉዓላዊነት ክብር በቁርጠኝነት የሚቆም የድል ሠራዊት አለን።

ይህ ሠራዊት የነፃነታችን ታማኝ ጠባቂ ሆኖ ዛሬም ነገም በጀግንነቱ እና በአሸናፊነቱ ደምቆ ኢትዮጵያን ወደ ላቀ ከፍታና ለቀጣዩ ትውልድ ያሻግራል።

#የመደመርመንግሥት

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: