በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዩጋንዳ አቻው ጋር 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።
በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ተቀይሮ የገባው ዘሚካኤል ምንያህል በ71ኛው ደቂቃ ኢትዮጵያን መሪ ያደረገች ግብ ከመረብ ቢያሳርፍም፤ አርኖልድ ካዬምባ በ78ኛው ደቂቃ ዩጋንዳን የአቻነት ግብ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በምድብ ሁለት በአራት ነጥብ በዩጋንዳ በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ምርጥ ሁለተኛ ሆኖ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።
ቡድኑ በመጀመርያ የምድብ ጨዋታው ቡሩንዲን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ድንቅ ጅማሮ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
በብሌን ደምበሎ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: