Search

የ"ማኅበራዊ ሚዲያን በአግባቡ በመጠቀም የሕዝቦችን አንድነት እና አብሮነት ማጠናከር ይገባል" - አቶ ፍቃዱ ፀጋ

ሓሙስ ጥቅምት 05, 2019 48

"በኢትዮጵያ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የፖሊሲ ትኩረት አስፈላጊነት" በሚል ጭብጥ በተጠና ሀገራዊ የዳሰሳ ጥናት ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ የቀረበው የዳሰሳ ጥናት እንደሚያመላክተው በኢትዮጵያ የኢንተርኔት እና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል።

ማኅበራዊ ሚዲያ በአግባቡ እና በኃላፊነት ስሜት ጥቅም ላይ ሲውል በርካታ አዎንታዊ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እሴቶችን የሚያስገኝ ቢሆንም፤ ባልተገባ መልኩ ሲያዝ ደግሞ ከፍተኛ ፈተናዎችን እና ስጋቶችን ደቅኖ መምጣቱ ተመልክቷል።

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ፀጋ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ ብዝኃ ባህል፣ ማንነት እና ሃይማኖት ያሏት ታላቅ ሀገር በመሆኗ፣ ማኅበራዊ ሚዲያን በእነዚህ እሴቶች መካከል የጋራ ትርክት በመገንባት እና አብሮነትን በማጎልበት ረገድ በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ገልጸዋል።

ሀገራዊ አንድነትን እና ሕዝባዊ ትስስርን በሚያጠናክሩ በጎ ጉዳዮች ላይ ማኅበራዊ ሚዲያው ሚናውን እያሳደገ መሄድ እንዳለበት ያመላከቱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ከዚሁ ጎን ለጎን በዘርፉ የሚደረጉ የፖሊሲ ማዕቀፎችን እና ተቋማዊ ቁጥጥሮችን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።

#የመደመርመንግሥት #ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ

በዓባዲ ወይናይ

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: