የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ እየጨመረ የመጣውን የ130 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ሕዝብ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፍላጎት በቀጣይነት ማሟላት የብሄራዊ ጥቅም ጉዳይ መሆኑን ገለጹ።
የብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር ኢትዮጵያ ወደ የባሕር በር ያስፈልገኛል ማለቷ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የሕልውና ጉዳይ መሆኑን ጠቁመዋል።
በቀይ ባሕር፣ በሰሜን ሕንድ ውቅያኖስ እና በባብ ኤል መንደብ አካባቢዎች የሚከሰቱ የደኅንነት ስጋቶችንና አደጋዎችን ከኢትዮጵያ በላይ በባለቤትነት የሚከላከልና የሚመክት ጠንካራ ኃይል በቀጣናው እንደሌለም ዋና አዛዡ ተናግረዋል።
በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚታዩ ድክመቶች ለቀጣናው ዋስትና መሆን የማይችሉ ሁኔታዎች እንደሚታይ ጠቁመው በእነዚህ የውሃ አካላት ላይ የሚፈጠር ማንኛውም ቀውስ የኢትዮጵያን ደኅንነትና ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ የሚጎዳ ነው ብለዋል።
በመሆኑ ኢትዮጵያ ለራሷም ሆነ ለቀጣናው ሰላምና ደኅንነት ዋስትና የመሆን ታሪካዊ ኃላፊነት እንዳለባት አስረድተዋል።
የኢትዮጵያን ባሕር ኃይል አቅም በከፍተኛ ደረጃ ማጠናከር ምርጫ ብቻ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ መሆኑን አንስተው፣ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር አካባቢ አዎንታዊ ሚና መጫወቷ የማይቀር እና ጊዜው እጅግ እየቀረበ የመጣ ተግባር መሆኑን ዋና አዛዡ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
በሃና ምንዳሁን
#የመደመርመንግሥት
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: