Search

ኢትዮጵያ በተመድ የምግብና እርሻ ድርጅት የ“100 Women Heroes” መድረክ፣ ዓለም አቀፍ ዕውቅና አገኘች

ሓሙስ ጥቅምት 05, 2019 68

የተባበሩት መንግሥታት የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) በግብርና እና ምግብ ሥርዓት እንዲሁም በገጠር ልማት ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ዕውቅና ለመስጠት ያዘጋጀው “FAO 100 Women Heroes” የተሰኘው ዓለም አቀፍ የዕውቅና መርሃ-ግብር በዛሬ ዕለት በጣሊያን ሮም በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት ተካሂዷል።

በመርሃ-ግብሩም ኢትዮጵያዊቷ ወ/ሮ ሰናይት ገዛኸኝ በግብርና እና የምግብ ሥርዓትን በማጠናከር፣ የገጠር ልማትን በማሳደግ እና የማኅበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል ረገድ ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ ዕውቅና ማግኘታቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የዕውቅና ሽልማቱንም የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር Dr. Qu Dongyu ያበረከቱላቸው ሲሆን ይህ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ኢትዮጵያዊያን ሴቶች በግብርና እና ምግብ ሥርዓት፣ በገጠር ልማትና በማኅበረሰብ ለውጥ ላይ ያላቸውን ጉልህ ሚና የሚያሳይ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ይህም ስኬት ኢትዮጵያ በግብርና እና ምግብ ሥርዓት ዘርፍ ያላትን አዎንታዊ አስተዋጽኦ በዓለምአቀፍና በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ መድረኮች አጉልቶ ከማሳየቱም ባሻገር ሀገራችን በግብርናው ዘርፍ ያላትን ልምድና ተሞክሮ ለዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ ለማስተዋወቅ ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብሏል።

ወ/ሮ ሰናይት ገዛኸኝ በጋምቤላ ክልል፣ መንገሽ ወረዳ ኩሚ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በየተለያዩ የግብርና ልማት ዘርፎች ማለትም የቡና ምርትን እና የእንስሳት እርባታ ኢንተርፕራይዞችን በማቀናጀት ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የግብርና ቢዝነስ የገነቡ የግብርና ሥራ ፈጣሪ እና የህብረተሰብ ለውጥ ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከቱ የሚገኙ ሞዴል ስራ ፈጥሪ የልማት አርበኛ ናቸው።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: