Search

የካፍ ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን ባሕር ዳር ገባ

ቅዳሜ ጥቅምት 07, 2019 43

ኢትዮጵያ የ2028 አፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ያቀረበችውን ጥያቄ ለመገምገም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን በዚህ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ ይታወቃል።

ዛሬ የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትሩ አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) እና የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታው አቶ መኪዩ ሙሐመድ የካፍ ልዑክ ቡድንን ይዘው ባሕር ዳር ገብተዋል።

ባሕር ዳር እና ኢንተርናሽናል ስታዲየሙ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ንድፈ ሐሳብ ስታቀርብ ካስመዘገበቻቸው ከተሞችና ስታዲየሞች ውስጥ ይገኛሉ።

በራሔል ፍሬው

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: