በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና ያደረጉት ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው 53ኛው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ 57ኛው ደቂቃ ላይ በፍቃዱ ዓለማየሁ እንዲሁም 62ኛው ደቂቃ ላይ ኡካይ ጁል ያስቆጠሯቸው ግቦች ኢትዮጵያ ቡናን 2 ለ 0 መሪ አድርገው ነበር።
82ኛው ደቂቃ ላይ አማኑኤል ኤርቦ ያስቆጠራት ግብ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሽንፈት አልታደገችም።
በጨዋታው በረከት ወልደዩሃንስ እና በፍቃዱ ዓለማየሁ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ያሬድ የማነ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በቀይ ካርድ ከሜዳ ሰናብተዋል።
በዚህም ኢትዮጰያ ቡና በ11ኛ የሸገር ደርቢ ድሉን የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ሦስት ነጥብ ሲያስመዘግብ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ በመጀመሪያው ሳምንት ያስመዘገባትን 1 ነጥብ እንደያዘ ወደ 3ኛው ሳምንት ተሸጋግሯል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: