የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ኢዮብ ተካለኝ (ዶ/ር) “ትልቅና የተሻሉ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር አፈጻጸምን ማፋጠን” በሚል ርዕስ በተካሄደው የሚኒስትሮች ውይይት ላይ ተሳትፈዋል።
በውይይቱም ወቅት ኢትዮጵያ የምታገኘውን የልማት ፋይናንስ ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ዕድሎች ለመለወጥ ያላትን ጽኑ አቋም አብራርተዋል።
የብሔራዊ ባንክ ገዢው ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ጋር ያላትን አጋርነት መሠረት በማድረግ፣ የልማት ውጤቶችን ለማፋጠን የፕሮጀክቶችን ዝግጁነት ማሻሻል፣ የአፈጻጸም ሂደቶችን ማቀላጠፍ እና የተቋማትን አቅም ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል።
በተጨማሪም የልማት ፋይናንስ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ድህነትን በመቀነስ እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትን በማረጋገጥ በኩል ትርጉም ያለው ውጤት እንዲያስገኝ ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ጋር በቅርበት ለመሥራት ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: