Search

ታምራት ቶላ የቤጂንግ ማራቶን ክብረወሰን ሰብሮ ሲያሸንፍ አንቺንአሉ ደሴም ድሏን ደግማለች

እሑድ ጥቅምት 08, 2019 51

የኢትዮጵያ አትሌቶች በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ያላቸውን ድል አድራጊነት እና ልዩ አቅም በድጋሚ ባሰመሰከሩበት የ2026 የቤጂንግ ማራቶን ውድድር፤ የፓሪስ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊው አትሌት ታምራት ቶላ አዲስ ክብረወሰን በማስመዝገብ በበላይነት አጠናቋል።

የ35 ዓመቱ አትሌት ታምራት ቶላ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ03 ደቂቃ ከ10 ሰከንድ በሆነ ጊዜ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ የቀድሞውን የውድድሩን ክብረ ወሰን በአራት ደቂቃዎች በማሻሻል ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል።

አትሌቱ በአውሮፓውያኑ 2023 በሻንጋይ ማራቶን በኬንያዊው ፊሊሞን ኪፕቹምባ ተይዞ የነበረውን የ2:05:35 ሰዓት በመስበር በመላው ቻይና ምድር በማራቶን ውድድር የተመዘገበ የምንጊዜም ፈጣኑ ሰዓት ባለቤት መሆን ችሏል።

በውድድሩ የሽልማት ደንብ መሰረት አትሌት ታምራት ቶላ ለአንደኛ ደረጃ የተዘጋጀውን 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም የቦታውን ክብረወሰን በመስበሩ ተጨማሪ 60 ሺህ የቻይና ዩዋን ጨምሮ በአጠቃላይ ወደ 59 ሺህ ዶላር የሚጠጋ የገንዘብ ሽልማት ተረክቧል።

በሌላ በኩል በሴቶች በተካሄደው ውድድርም ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አንቺንአሉ ደሴ ውድድሩን በ2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ36 ሰከንድ በማጠናቀቅ በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ የቤጂንግ ማራቶን አሸናፊ በመሆን የ50 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ሆናለች።

የኢትዮጵያ አትሌቶች በቻይና መዲና ያስመዘገቡት ይህ ታላቅ ድል የሀገራችንን ስም ከፍ ያደረገ እና #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ ማሳያ የሆነ ድንቅ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የስፖርት ከፍታ ሆኖ ተመዝግቧል።

 

በእሱባለው ተሾመ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: