Search

ማንቸስተር ዩናይትድ ከሊድስ ዩናይትድ ጋር 1 ለ 1 ተለያየ

እሑድ ጥቅምት 08, 2019 56
በሰባተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ኤላንድ ሮድ ስታዲየም አቅንቶ ሊድስ ዩናይትድን የገጠመው ማንቸስተር ዩናይትድ 1 ለ 1 ተለያይቶ የውድድር ዓመቱን አራተኛ የአቻ ውጤት አስመዘግቧል።
ማንቸስተር ዩናይትድ በመጀመሪያው አጋማሽ 35ኛው ደቂቃ ላይ ብሪያን ምቡሞ ባስቆጠራት ግብ ቀዳሚ ቢሆንም፣ 51ኛው ደቂቃ ላይ ዶሚኒክ ካልቨርት ልዊን ያስቆጠራት ግብ ሊድስ ከጨዋታው ነጥብ ተጋርቶ እንዲወጣ አስችላለች።
ውጤቱን ተከትሎ ከሰባቱ ሳምንታት ጨዋታዎች አንድ ጊዜ ብቻ ያሸነፈው ማንቸስተር ዩናይትድ በሰባት ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፣ ሊድስ ዩናይትድ በ10 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።
በሌላ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስን 5 ለ 0 የረታው ብራይተን ነጥቡን 16 በማድረስ ሁለተኛ ደረጃን በጊዜያዊነት ተረክቧል።
ቦርንማውዝ ሰንደርላንድን 2 ለ 0 የረታበት ሌላኛው የዛሬ መርኃ ግብር ነው።
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: