Search

በአፈ-ጉባኤዎች መካከል የሥራ ርክክብ ተደረገ

ዓርብ መስከረም 29, 2019 70

7ኛው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አህመድ ሽዴ ከቀድሞው አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ጋር የሥራ ርከከብ አድርገዋል።

አፈ-ጉባኤ አቶ አህመድ ሽዴ በዚሁ ወቅት፣ ምክር ቤቱ ታላቅ የሥራ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን አንስተዋል።

የቀድሞው አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የቀድሞዋ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ባለፉት ዓመታት የተጣለባቸውን ምክር ቤታዊ ኃላፊነት በቅንነት፣ በታታሪነት እና በመግባባት መንፈስ መወጣታቸውን ገልጸዋል።

ሁለቱም አፈ-ጉባኤዎች ለሕዝባቸውና ለሀገራቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ አፈጉባኤው አመስግነዋል።

በቀጣይም ምክር ቤቱ የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አፈ-ጉባኤ አቶ አህመድ ሺዴ ተናግረዋል።   

የቀድሞው አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የቀድሞዋ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በምክር ቤት ቆይታቸው የተለያዩ ተግዳሮቶችን በመወጣት የሪፎርም ሥራዎችን ጨምሮ በርካታ ተግባራትን ማከናወናቸውን አብራርተዋል።

በምክር ቤቱ በነበራቸው ቆይታ ምክር ቤቱን እና የምክር ቤቱ ጽ/ቤት አመራሮችን በማመስገን፤ የ7ኛው ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

በሥራ ርክክቡ ወቅት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አየለች እሸቴ እና የምክር ቤቱ ጽ/ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: