Search

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገውን በረራ ጀመረ

እሑድ ጥቅምት 01, 2019 53

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ዛሬ ጀምሯል።

የአየር መንገዱ አውሮፕላን ዛሬ ማለዳ መቐለ ከተማ ማረፉን እና አየር መንገዱ ወደ ትግራይ ክልል በረራ መጀመሩን ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎች በአሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ደስታቸውን እየገለጹ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረውን ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚጀምር መሆኑን መግለጹ ይታወቃል።

#የመደመርመንግሥት

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: