Search

የኢሬቻ በዓል በተለያዩ አካባቢዎች በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል

እሑድ ጥቅምት 01, 2019 59

በዓሉ በተለያዩ መልካዎች "ኢሬቻ ለብሔራዊ መግባባት" በሚል መሪ ቃል በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።

በዚህም መሠረት በሸገር ከተማ በቡራዩ የመልካ አቴቴ፣ በሰበታ የመልካ ሰበታ እንዲሁም በገላን የመልካ ጨፌ ቱማ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሯል።

በተመሳሳይም "ኢሬቻ ለብሔራዊ መግባባት" በሚል መሪ ቃል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ የመልካ አሶሳ የኢሬቻ በዓል በድምቀት ተከብሯል።

የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ሕዝብ ማንነት፣ ባህል እና እሴት መግለጫ የሆነ የምሥጋና፣ የእርቅ፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የጋራ አብሮነት መድረክ ነው።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: