Search

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

ማክሰኞ ጥቅምት 03, 2019 60

ዛሬ በ45ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ተገኝቻለሁ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በታሪክ፣ በቅርስ፣ በትምህርት፣ በማኅበራዊ ኑሮ፣ በደን ጥበቃ፣ በአጠቃላይ በሀገረ መንግሥት ግንባታ ያበረከተችው አስተዋጽዖ ምትክ የለሽ ነው።

ይሄንን ዕምቅ ዐቅም በመጠቀም ድህነትንና ኋላ ቀርነትን ለማጥፋት፣ ሰላምን ለማጽናት እና ሕዝቦችን ለማስተሣሠር ግንባር ቀደም ሚና እንደምትጫወት ተስፋ አደርጋለሁ።

የሃይማኖት ተቋማት መንፈሳዊነትን ኃይል አድርገው ለሀገር ግንባታ በሚያደርጉት አስተዋጽዖ ሁሉ መንግሥት አብሯቸው ለመሥራት ዝግጁ ነው።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: