Search

በሞተር ብስክሌት ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳ

ማክሰኞ ጥቅምት 03, 2019 54

በመዲናዋ አዲስ አበባ ሞተር ብስክሌትን በመጠቀም ወንጀል የመፈፀም፣ የተሰረቁ እቃዎችን ከቦታ ቦታ የማዘዋወር፣ የመንገድ ትራፊክ ሕጎችን የመጣስ የደንብ ጥሰቶች እየተፈጸሙ መሆናቸውን በመግለፅ ከመስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ባለ ሁለት እግር ሞተር ብስክሌት በአዲስ አበባ ማሽከርከር መከልከሉ ይታወቃል።

በአሽከርካሪዎቹ በስፋት ከሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶች መካከል በተለይ ቀይ መብራትን መጣስ፣ ሌሎች ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ማምለጥ፣ ሄልሜት ሳያደርጉ ማሽከርከር፣ የተፋፋቀ እና ለእይታ አስቸጋሪ የሆኑ የሠሌዳ ቁጥሮችን መጠቀም ወ.ዘ.ተ. ይገኙበታል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ሕግን የማስከበር ስልጣንና ኃላፊነቱን በመጠቀም ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርግ አሳስቦ፣ የሞተር ሳይከል መንቀሳቀሻ ፈቃድ ያላቸው እና መንቀሳቀሻ ፈቃድ ያደሱ ሞተር ሳይከል አሽከርካሪዎች ከነገ ጥቅምት 04 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 12:00 ሠዓት ጀምሮ የትራንስፓርትና የትራፊክ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የወጡ ሕጎችን አክብረው እንዲንቀሳቀሱ የተፈቀደ መሆኑን አስታውቋል።

ዋና ጠቅላይ መምሪያው የመንቀሳቀሻ ፈቃድ የሌላቸው እና ፈቃድ ሳያድሱ በሚንቀሳቀሱ የሞተር አሽከርካሪዎች ላይ በሕግ አግባብ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አሳስቧል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: