ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ እና በባለብዙ ወገን የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይቱን በማስመልከት በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ያካሄዱት ውይይት በኢትዮጵያ እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን ዕድሜ ጠገብ ወዳጅነት ወደ ላቀ ስትራቴጂያዊ እና ተግባራዊ አጋርነት ለማሳደግ በሁለቱም ሀገራት በኩል ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት ያረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል።
አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ በተመለከተ የሰጠችውን ማረጋገጫ ያደነቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር እንዲሁም በቀጣናዊ እና ባለብዙ ወገን መድረኮች ቅድሚያ በሚሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ በቅንጅት ለመሥራት ኢትዮጵያ ያለባትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: