Search

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል

ረቡዕ ጥቅምት 04, 2019 90

የኢፌዴሪ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ1ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ 3ኛ መደበኛ ስብሰባው ነገ ጥቅምት 5 ቀን፣ 2019 ዓ.ም ያካሂዳል፡፡

ምክር ቤቱ በነገ መደበኛ ስብሰባው በህገ- መንግስቱ አንቀጽ 55/19/ እና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ስነምግባር ደንብ ቁጥር ቁጥር 6/2008 አንቀጽ 152 መሰረት የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

እንዲሁም በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ስነምግባር ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀጽ 4/1/ (መ) እና አንቀጽ 5/4/(መ) መሰረት የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት ለመወሰን የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴዎች ዕጩ አመራር እና አባላትን ምደባ አስመልክቶ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ የሚያፀድቅ ይሆናል፡፡

#የመደመርመንግሥት #ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ

#Ethiopia #EBC #HOPR

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: