Search

የሕገ ወጡ ህወሓት ቡድንን የጥፋት ዕቅድ እያከሸፈ ያለው የትግራይ ሕዝብ ጽኑ የሰላም አቋም

ረቡዕ ጥቅምት 04, 2019 84

ሕገ-ወጡ የህወሓት ቡድን ለሥልጣን ጥሙ ሲል ከውጭ አካላት ጋር በመተባበር ሕዝብን ለጦርነት እና ለሰቆቃ ለመዳረግ ያደረገው ጥረት የትግራይ ሕዝብ ለሰላም ባሳየው ጽኑ አቋም እየከሸፈ ነው።

ሕዝቡ የቡድኑን እውነተኛ ማንነት ከጊዜ ወደ ጊዜ በመረዳት ለጥፋት ሴራው በስሙ እንዳይነግድ የፀና ቁርጠኝነቱን አሳይቷል። የካይሮ አለቆቹን ፍላጎት ለማስፈፀም ሲል የነፃነት ታጋይ ነኝ በሚል የዳቦ ስም ሲንቀሳቀስ የቆየው ሕገ ወጡ ህወሓት፣ ባለፉት 50 ዓመታት በላይ አዲስ ሐሳብ እና ለውጥ መቀበል አለመቻሉን የፖለቲካ ተንታኞች ያስረዳሉ።

ወጣቶችን በግዳጅ አፈሳ ወደ ጦር ግንባር በመንዳት የሕዝብን ሰቆቃ ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋል የዚሁ ቡድን ዘወትር መገለጫ ነው፤ ይህንንም እንደ አሰግድ ገብረሥላሴ “ገሃዲ” መጽሐፍ ያሉ ታሪካዊ ሰነዶች የቡድኑን የግዳጅ አፈሳ፣ የውስጥ አፈና እና ግፍ በግልጽ ያጋልጣሉ።

የኢፌዴሪ መንግሥት ወደ ጦርነት የመግባት ፍላጎት እንደሌለው በተደጋጋሚ ቢያስገነዝብም፣ የጥፋት ቡድኑ አሮጌውን የጦርነት ስትራቴጂ ማራመዱን ቀጥሏል።

ዛሬ ላይ የትግራይ ሕዝብ የህወሓትን እውነተኛ ማንነት እና የውሸት ትርክት ሙሉ በሙሉ ተረድቷል። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ወደ ክልሉ ሲገባ የተደረገው ደማቅ አቀባበል የሕዝቡን ጥልቅ የሰላም ናፍቆት የሚያሳይ ነው።

መቐለ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ የተመለሰች ሲሆን፣ ሕዝቡ ከጦርነት እና ከጥፋት አዙሪት ወጥቶ በልማት እና በሰላም ለመኖር ያለውን ፍላጎት በአደባባይ አሳይቷል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳም የህወሓትን ዳግም ጦርነት ቀስቃሽ መንገድ ማውገዛቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ቀዳሚ እና ብቸኛ ምርጫ ሰላም፣ ልማት እና የሀገር ብልጽግና ነው፤ የውጭ ሴራዎች እና የውስጥ ተላላኪዎች የጥፋት እቅድ በሕዝብ አንድነት፣ በሠራዊቱ ፅናት እና በሰላም አማራጭ ሙሉ በሙሉ ከሽፏል።

#የመደመርመንግሥት

በመሐመድ ፊጣሞ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: