Search

አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችበት "IMEX America 2026" የማይስ ቱሪዝም ኤክስፖ በላስ ቬጋስ፣ ኔቫዳ ተከፈተ

ሓሙስ ጥቅምት 05, 2019 43

ይህ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ንግድ ኤክስፖ፣ በዓለም ቀዳሚ ከሆኑ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ኤክስፖ አንዱ ሲሆን፣ ከ150 በላይ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ ከ3 ሺህ 700 በላይ ተሳታፊ ድርጅቶችን ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዚህ ታላቅ የማይስ ቱሪዝም ኤክስፖ ላይ በመተሳተፍ የከተማዋን የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዕድሎች እና የቱሪዝም ሀብቶችን ለዓለም እያስተዋወቀ ይገኛል።

አዲስ አበባ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ አለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ኮንፍረንሶችን በማስተናገድ በአፍሪካ ግንባር ቀደም ከሆኑ የኮንፍረንስ ቱሪዝም መዳረሻዎች መካከል አንዷ ናት።

እንዲህ ዓይነቱ የቱሪዝም ንግድ ኤክስፖ ይበልጥ የከተማዋን የቱሪዝም ሀብት ለማስተዋወቅ እና በዘርፉ ካሉት ተዋናዮች ትሥሥር ለመፍጠር የሚያግዝ መሆኑን ከአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#የመደመርመንግሥት       

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: