Search

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አመራሮችን እና የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ አባላትን ሾመ

ሓሙስ ጥቅምት 05, 2019 65

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም የቋሚ ኮሚቴዎችን ዋና እና ምክትል ሰብሳቢዎችን ሾሟል።

በዚህም መሠረት 13 አባላት ያሉት የምክር ቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ አባላት እና ለ13 ቋሚ ኮሚቴዎች የሚያገለግሉ 26 ዋና እና ምክትል ሰብሳቢዎች ተሰይመዋል።

ምክር ቤቱ አባላቱን እና የኮሚቴ አመራሮቹን የሰየመው የትምህርት ዝግጅትን፣ የተፎካካሪ ፓርቲዎችን ተሳትፎ እና አካታችነትን መሠረት በማድረግ መሆኑ ተገልጿል።

ይህም መንግሥት ዲሞክራሲያዊ መግባባትን ለመገንባት፣ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመንግሥት አስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶችና በምክር ቤት ያላቸውን ሚና ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት የሚያሳይ እንደሆነ ተመላክቷል።

#የመደመርመንግሥት

በመስከረም ቸርነት

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: